Message from The Lay Pastor

What a journey, the Medhane Alem Evangelical Church of OC, has come through!
Even in its weakest moments, when worldliness and carnality heats hard on its walls, when the assault of the enemy is intense and felt like the ship is falling apart, the Church of God has continued to be a witness to the great love and grace of our Lord Jesus as displayed on the cross so also is the story of MAEC of OC. Through it all, I marvel how week after week the Lord poured His grace, granted His presence and restored our fellowship to worship Him in spirit and truth, to hear His Word and be comforted and built up in faith! It's an honor and a personal commitment to always serve our Lord and Savior Jesus Christ and the part of His body in OC for past several years along with the elders, the ministry leaders and everyone in the congregation.
I believe MAEC is shaping up beautifully to continue functioning as a living organism and is better structured as an organization to spread the good news of salvation through faith in our Lord Jesus, provide discipleship to the believers and reach out our Ethio-Eritrean community in Southern California with basic needs.
To God be all the glory and praise.
May the Lord bless and keep you as you endeavor to fulfill the great commission in a locality He has assigned for you for a season.

Wesenachew Asfaw

"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”
        ማቴዎስ 11፥28-30

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይኼንን ጥሪ ያቀረበው ቁሳዊ ሸክም ተሸክመው በፊቱ ለቆሙ ሰዎች አልነበረም። በትከሻቸው ላይ የተጫነ በእጃቸው የተንጠለጠለ ሸክም ባይኖርም በነፍሳቸው ላይ ተደላድሎ የተቀመጠ ትልቅ የኃጢአት ሸክም ግን ነበረባቸው። ይኼ ሸክም የወደቀባቸው ሰዎች ደካሞች መሆናቸው አስገራሚው ተቃርኖ ነበር። በተለምዶ ሸክም የሚሸከሙ ሰዎች ብርቱ የሚባሉ ቢሆኑም እነኚህ ግን ደካሞች ናቸው። ሸክሙን በላያቸው ለመጫን ያገኙት ጉልበት ሸክሙን ከጫንቃቸው ላይ ለማውረድ አልረዳቸውምና የሚያሳርፋቸው ሽተው ሲቅበዘበዙ ነበር። እነዚህ ሰዎች ሊያደርጉ የሚችሉት አንድ ነገር ብቻ ነበር፤ ወደ ኢየሱስ መምጣት። ለነዚህ ሰዎች ከተደረገው ጥሪ በተጨማሪ ወደ እርሱ ለሚመጡ ሰዎች የተሰጠው የተረጋገጠ የእረፍት ተስፋ ነበር።
ዓለማችን የኃጢአት ሸክም የተጫናቸው ደካማ ሰዎች  የሚኖሩባት ሥፍራ ነች። ሰዎች ወደው በነፍሳቸው ላይ የጫኑትን ሸክም የሚያነሳላቸው አካል ፍለጋ በተለያዩ ሥፍራዎች  በመባዘን ላይ ናቸው። እነዚህን ሰዎች ያርፉ ዘንድ ይኼንን የምስራች የሚነግራቸው ይሻሉ። ጌታችን ኢየሱስ ይኼንን ጥሪውን በየዘመኑ ታሰማለት ዘንድ በምድር ላይ ቤተ ክርስቲያኑን መስርቷል።  ተልዕኮውን ማስፈጸሚያ መንፈሱንም ሰጥቷል። የቀረው የቤተ ክርስቲያን ድርሻ ነው። ሸክም ለተሸከሙ ደካሞች የምስራች ማወጅ። ጌታ "ማንን እልካለሁ ማንስ ይኼድልናል?" (ኢሳ. 6፥8) እያለ ነው።  በሆነ ወቅት በላያችን ስለነበረው ነገር ግን በጌታ ይቅርታ ከላያችን ተገፍትሮ ስለወደቀው ኃጢአታችን ባሰብን ጊዜ ሁሉ ስላዳነን ሞትና ትንሳዔው ጌታን እናመሠግናለን።ነገር ግን ከዚህ ሸክም ጋር የሚኖሩ ደካሞች እርዳታችንን ይጠባበቃሉ። መልካሙን የምስራችን የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው (ሮሜ 10፥15) እንዲል ቃሉ እግሮቻችንን አፍታተን አንደበታችንን ከፍተን የእረፍቱን ጥሪ ይዘን እንውጣ። ጌታም ይረዳናል!

ፓስተር ዮሐንስ አባተ

Message from The Pastor

Sunday Service

የቤተክርስቲያን የሰንበት አገልግሎት

  • Regular Sunday Service

    9:30-10:30 AM Prayer

    10:30 AM - 12:30 PM Sunday Worship Service

  • Children Sunday School (ሰንበት ትምህርት)

    11:00 AM - 12:30 PM

  • Youth Worship Service

    10:30AM-12:30 PM

Do you need prayer?

እንዲጸለይልዎት ይፈልጋሉ?

Call 323-839-1212

Do you need prayer? እንዲጸለይልዎት ይፈልጋሉ? Call 323-839-1212

Dream it

Do you need prayer? እንዲጸለይልዎት ይፈልጋሉ? Call 323-839-1212 Dream it